በ SPS አሁን ይመዝገቡ!
Summary : ጅዎ ነሐሴ 31 ላይ 5 ዓመት ይሆነዋል(ይሆናታል)? ስለዚህ በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ወደ ኪንደርጋርተን ለመመዝገብ ጊዜው አሁን ነው።!
![A student smiles for a photo with a sign that says welcome in Amharic](http://2oqd.gabonmagazine.com/wp-content/uploads/2022/03/SWS-am-IMG_1561-150x150.jpg)
የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS)
እንኳን ወደ ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በደህና መጡ! ወረዳችን ወላጆች ታላላቅ የትምህርት ባለሙያዎችን : ጠንካራ የትምህርት ፕሮግራሞችንና ተሳታፊ ማህበረሰብ የሚያገኙበት የአካባቢና አማራጭ ት/ቤቶች ያሉት ነው::
ተማሪዎቻችን ቅድሚያ ይሰጣቸዋል
በ SPS, ዋናው ስራችን ጸረ-ዘረኝነትን የሚያራምድ የትምህርት ስርዓትን የሚያማክል የተማሪዎች ትምህርትን በመደገፍ እያንዳንዱ ተማሪ ለኮሌጅ፣ ለስራ እና ለህይወት ዝግጁ ሆኖ እንዲመረቅ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ የኛ ኃላፊነት እንደሆነ እናምናለን።
በሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ይመዝገቡ!
ነሃሴ 31 ላይ ልጅዎት 5 ዓመት ይሞላዋል/ይሞላታል? ቤተሰብዎ ለሲያትል አዲስ ነው? ከሆነ ለትምህርት ቤት የመመዝገቢያው ጊዜ አሁን ነው!
ቀደም ብለው በመመዝገብ፣ ተማሪዎች በክፍት የምዝገባ ወቅት (ከፌብሩዋሪ 1-28) አስፈላጊ ግብዓቶችን እና ከተመደቡበት የመማሪያ ትምህርት ቤት ውጪ ላሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶች የማመልከት እድል ያገኛሉ።
ለመጪው የት/ዘመን አዲስ የተማሪ ምዝገባ ጃንዋሪ 3 ይጀመራል::
ልንረዳዎት እንችላለን:: የቋንቋ ድጋፍ በ ስፓኒሽ: ኦሮሞ: ቻይንኛ: ቬትናሚዝ: አማርኛ እና ሶማሊ ይኖራል:: በ ጆንስታንፎርድ አድራሻችን 2445 3rd Ave S, Seattle, 98134 ይጎብኙን::
ሰዓት: ከሰኞ – ዓርብ: ጥዋት ከ9:00 ሰዓት – ከሰዓት በኋላ 5:00 ሰዓት
ጥያቄ ወይም አስተያየት አልዎት? በ admissions@gabonmagazine.com ወይም በ 206-252-0760 ያግኙን::